Skip to main content

 

የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፊ ዋና ዋና ግቦች

  • ከዘርፎች ጋር በቅንጅት መስራት
  • ት/ቤቶች የሚያገኙትን  ገብ በአግባቡ እንድጠቀሙ  በመመሪያዎች ላይ ግነዛበ መስጠትና መደገፊ
  • ከቢሮ ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የት/ቤቶች ግነባታን በአግባቡ መደገፍነና የክፊል ተማር ጥምረታዎችን ማስተካከል
  • የት/ት ብክነት እነዳይከሰት መመርያዎችንና ድነቦችን ተግባር እንሆኑ መከታተል
  • በ ሁሉም ት/ቤቶች  የሚገኙ ተማርቸዎች ልዩ ፍላጎት ያላቸዉ ጨምሮ ፆታዊ ልዩነት እንዳይኖር በማድረግ ማስራት
  • ለት/ት ጥራት የሚሆኑ ሀብቶችን ከመነግሰተሰት፣መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከህዘብ የሚሰበሰቡት ለታለመለት ዓላማ ላይ እድዉል መከታተልና መደገፍ
  • ጥራት ያለዉ መረጃ በመሰብስብና በመትነትነ ወቅቱን በመጠበቅ ለሚመለከተዉ አካል ማስተላለፍ
  • የመ/ርን ጥቅማጥቅም በተቀመጠዉ መመርያ መሰረት ተገባራዊ እድሆን መስራትና መከታተል
  • ግዠዎችና ወጭዎች በጥራት በወቅትና በታቀደዉ ልክ እድፈፀም በትኩረት ይሠራል
  • ለማህበረሰቡ ጥራት ያለዉ ት/ት ለማድረስ ጠናማ የሆነ ማህበረስብ እነድኖር ኤ.ች.ቨ ኤድስ ለመከላከል ጠንካራ የግንዛበ ሥራ መስራት
  •  ጥራት ያለዉ ት/ት ለማረጋገጥ በሙያዉ የታመነ ፤በሥነ ምግባር የታነፀ ባለሙያን በግለፀኝነትና በፍታዊነት መቅጠር
  • የት/ቤቶች አመራር በብቃታቸዉና በዉጠታቸዉ መሠረት እንድመደቡ በትጋት ይሠራል

1 የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ሥራውን ውጤታማ ማድረግ                            

• የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣

• ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣

• የተቋሙን ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፣

• በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣

• በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣

• አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣

• የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣

2 የመምራንና የትም/ት አመራር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

 በመከታተልና በመገምገም ሥራውን ውጤታማ ማድረግ፣

• የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣

• ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣

• በሴክተሩ የሚገኙ ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያካናውናል፣

• በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በመምህራን፣ በትምህርት አመራርና በሠራተኞችአስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣                                                                  

• የመምህራን፣ የትምህርት አመራርና ሌሎች ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች በማዘጋጀትና በማሻሻል በሴክተሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ድልድል/ ምደባ፣ ዝውውር የቅሬታ ማስተናገጃ እንዲሁም በሴክተሩ ለሌሎች ሠራተኞች ደግሞ ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣

• አዲስ ለሚደለደሉ/ ለሚቀጠሩ ዕጩ መምህራንና የትምህርት አመራር/ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣

የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል  ግምገማ ዳይሬክቶሬት   

  • የትምህርት ሴክተሩን ፖሊሲንና ስትራቴጂ መነሻ ያረገ የትምህርት ልማት ዕቅድና ሪፖርት ማዘጋጀት
  •  በበጎ አድራጊዎችና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ  በተገኘ ገነዘብ የሚገነቡ ግንባታዎች በወቅቱነና በጥራት ተሰርቶ መጠናቀቁን መከታተል ማረጋገጥ
  •   የበጀት  ስረዓትን ማስተዳደር
  •    በመንግስት በሚመደብ መደበኛና ካፒታል በጀት የሚሰሩ ስራዎች ወይም ተግባራት አፈጻጸምን በማሻሻል የሴክተሩን አቅም ማጎልበት
  • ከማሕበረሰብና መንግሰታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሀብት በማፈላለግ የሴከተሩን አቅም ማጎልበት
  • መንግስታዊ ላልሆኑ የበጎ አድራጎት ተቀማት አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ
  •  በትምህርት ላይ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ተቀማትና ማህበራትን መደገፍና መከታተል  
  • የትምህርት ሴክተሩን የዕቅድ አፈጻጸም መከታተልና መገምገም 

የዘርፈ ብዙ ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት

በክፍሉ የምሰሩ ሥራዎች

  • የትምህርት ማህበረሰብናለሎች ዘጎች በኤች.አይ.ቪ/ኤዲስ እና በአባላዘር በሽታ እንዳይያዙና እንዳይጠቁ ማስተማር ወይም ግንዛቤ መፍጠር፡፡
  • በሁሉም ትምህርት ቤት የተጠናከረና የተደራጀ የፀረ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ክበባትን ማቋቋምና ተንክረዉ መልዕክት እንድያሰተላልፉ ማድረግ፡፡
  • ኮንደም ማሰራጨት ፣ አጠቃቀምና አገልግሎቱን ማስተዋወቅ፡፡

የበሽታዉ መተላለፍያ መንገዶች

  • ሊቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት
  • ስለታማ ቁሳቁሶችን በጋራ በመጠቀም
  • የዉርስ ጋብቻ፣ድርብ ጋብቻ…….ወዘተ

በሽታዉን መከላከያ ዘደዎች        

  • ሊቅ የሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነትን(ዝሙትን) ማስወገድ
  • ስለታማ ቁሳቁሶችን በጋራ መጠቀምን ማስወገድ
  • 1 ለ1 ጋቢቻን ማጠናከር
  • ኮንደምን በአግባቡ መጠቀም

 ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በጋራ እንከላከል!!

የሴቶች ህፃናት ጉዳይ ማካተትና  ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት

በሥራ ሂደቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች

•  የሥራዓተ ጾታ ክፍተት መለየት

•  የማስፈጸሚያ መመሪያዎችን የአሰራር መኑዋሎችን ማዘጋጀት/መከለስ/

•  ስልጠናዎችን  ማዘጋጀትና መስጠት

•  በፈጻሚ አካላት መካከል ቅንጅት መፍጠር

•  ረቅቂ ዕቅዶችን ከሥርዓተ-ጾታ አንጻር መፈተሸ

•  ተሳትፎአቸዉን የሥርአተ ጾታ ኦዲት ማድረግ

•  በሥራ ሂደቱ አፈጻጸም ላይ ድጋፋዊ ክትትልና ግምገማ ማድረግ

•  በተጠቃሚ ደረጃ በሚመጣዉ ዉጤት ላይ መረጃዎቸወነወ ማዘጋጀትና ማዉጣት

 የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

በግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ውስጥ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች

  • በየወሩ ስራ ማስኬጃ ገንዘብ፡- ደመወዝ እንዲሁም ካፒታል፣ ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ከፋይናንስ ቢሮ ጠይቆ ማምጣት፤
  • ልዩ ልዩ መደበኛ በጀት፣ ካፒታል፣ ዩኒሴፍ፣ ዋን ዋሽ፣ ጂኲፕ እና ሌሎች እንዲህ አይነት ክፍያዎች መመሪያውና ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት መክፈል፤
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተቀናሽ ግብርና እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደራ ገንዘብ በመሰብሰብ ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው በማስተላለፍ ማስረጃ መውሰድ፤
  • ወሩ በገባ በ25ኛው ቀን ለሰራተኞች የሚከፈል ፔይሮል በማዘጋጀት ባንክ በመላክ ከ26ኛው ቀን ጀምሮ አፈጻጸሙን መከታተል፤
  • በየወሩ ተሰብሳቢ ሂሳብ በጊዜ መወርዱን መከታተል፤
  • የበጀት ዝውውር ስራ መከታተልና መመዝገብ፤
  • በየወሩ የሂሳብ ስራዎችን በመከታተል ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን የባንክን ሂሳብ መከታተል፤
  • በየእለቱ የሂሳብ ምዝገባ በአይቤከስ ሶፍትዌር በመመዝገብ ከቀኑ 10፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ በማስተካከል የማጣራት ስራ መስራት፤
  • የዜሮ ሚዛን ሪፖርት ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መላክ፤
  • በየወሩ ለኦዲት ስራ መረጃ በማዘጋጀት ሂሳቡ እንዲጣራ በማድረግ ስህተት ቢገኝ አፋጣኝ ማስተካከያ ማድረግ፤
  • ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በጀቱን በአግባቡ መክፈልና ስሌቱን ማውረድ፤
  • አመታዊ እቅድ በማሰባሰብ የግዢ እቅድ  ማዘጋጀትና ከሐምሌ 1-30 ባለው  ጊዜ ውስጥ ለግዢ ኤጀንሲ መላክ፤
  • የግዢ ፍላጎት መሰረት በማድረግ እስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት፤
  • የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀትና ጨረታውን በአግባቡ ማጠናቀቅ፤
  • የቢሮን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው እቃ ገዝቶ ማቅረብ፤
  • የዋጋ ጥናት መረጃ ለሚፈልግ  ማቅረብ፤
  • ለተቋሙ ንብረት መለያ ቁጥር መስጠት፤
  • እቃዎችን በመልካቸው ለመለየት ስርአት ባለውና በጥሩ ሁኔታ መዝግቦ መከታተል፤
  • በሶስተኛው መጨረሻ አመት የንብረት ቆጠራ ማድረግ፤
  • የሚጠገኑና የሚወገዱ እቃዎችን በመለየት በመመሪያው መሰረት ማንሳት፤
  • ወደ ሳጥን የሚገባና የሚወጣ ሂሳብ በመከታተል መዝገቡን በመልኩና በጀቱን በርእሱ ለይቶ መመዝገብ፤
  • በየእለቱ ሳጥኑን ማስቆጠርና አስፈላጊ ሰነዶችን በደንብ መያዝ፤
  • የበጀት አመቱን የሂሳብ ሰነድ በወርና በበጀት ምንጭ ግዢና በሌላ በሌላ የክፍያ ሰነድ ለይቶ በሞዴል 42 መዝግቦ መስጠት ወይም መውሰድ፤
  • የግዢ አጠቃላይ ውል ማዘጋጀት፣ ማጽደቅና መረጃ መተንተን፤
  • የግዢ መረጃ በመልክ መልኩ በመለየት መመዝገብ፣ የግምገማ ውጤት በቦርድ ላይ መለጠፍና ለህዝቡ ይፋ ማድረግ፤
  • ጨረታ የሚከፈትበትን ስነ-ስርአት፣ ንብረት መቁጠርና የተበላሸውን ለይቶ የማስወገድ ስራ የስነ-ስርአት ክፍልና ከውስጥ ኦዲት ጋር በቅንጅት መስራት፤
  • የተቆጠረውን ንብረት መመዝገብ፤
  • ለለውጥ የታሰበውንና የቡድን ስራ ባህል ማሳደግ፤
  • የፈጻሚዎችን አቅም መገንባት፤
  • የልምድ ልውውጥ ማድረግ፤
  • ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፤

1  ስታትስቲክስና መልከአ-ምድራዊ ዳታ ስርዓት አስተዳደር ትንተና ስርጭትዳይሬክቶሬት