Skip to main content
G12 Result

በክልል የ2017 ትም/ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ 5.4 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ በማምጣት ማለፋቸዉንና ይህም ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር 63.6% መሻሻል ያሳየ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ በየነ ባራሳ ዛሬ የአመቱን ውጤት ይፋ ባደረጉበት መግለጫቸው አመላክተዋል።

በክልሉ የማሳለፍ ምጣኔ ከማሻሻልም በተጨማሪ የክልሉ ተማሪዎች የመወዳደር አቅም እየተሻለ መሆኑን የሚያሳዩ ውጤቶችም መመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን በመነሻ አካባቢ 11 የክልሉ ተማሪዎች ብቻ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሲሆን በዚህ አመት 72 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማለትም 500 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ መቻላቸውን አንስተዋል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያስፈተኑ ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ ካሳለፉ 50 ት/ቤቶች መካከል አንዱ በክልሉ የሚገኝ መሆኑን ያነሱት ሀላፊው ይበልጥ ከተጋን ከዚህ በብዙ እጥፍ ማሳካት የሚቻል መሆኑን አበክረው አሳስበዋል።

በሌላ በኩልም የመጣው መሻሻል አበረታች ቢሆንም ዉጤቱ አሁንም ዝቅተኛ በመሆኑ ቢሮው ለተሻለ ውጤት የሚያበቁ ሥራዎችን አቅዶ እየፈጸመ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ሁሉም በየፊናው በ2018 ዓ.ም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በላቀ ትጋትና ተነሳሽነት ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ለመጣው መሻሻል አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመስግነው ጠንካራ የትምህርት ስርአት ለምናስበው የትውልድ ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ ከትምህርት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ሁሉም አካላት የትምህርት ጊዜ ብክነት በማይኖርበት ሁኔታ የአመቱን የትምህርት ሥራ መፈጸም እንደሚገባ የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል።

ትም/ቢሮ