Qoqqowoomu 2018 Haaro Rosu Diri roso Hawaassi Quchumi Gashshoot Giddo Afantanno Rosi Minnara Leelle Hanafisiisnohu Kalaa Zegeyye Kuyisihu Biirote Borrote Mini Sooreessi Rosaanote,Rosiisaanotenna Rosu Maate Baalunkura Haaru Rosu Diri Sai Dirinni Roore woyyaawino Guma Maareekisiinseemmoha Ikkara Rosanna Rosiisate Harinsho Lende Kaajjisha Hasiissanota Kule Haaru Diri Qoqqowinkera Roore Gumma Maareekisinseemmoha Ikkara Halchosinna 2018Rosu Diri Faajjete Hanafamasi Xawisino.
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የ2018 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን የመማር ማስተማር ሥራ በይፋ ተጀመረ።
መስከረም 5/2018ዓ.ም/የቢሮው ህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶረት/
ክልላዊውን የ2018 ትምህርት ዘመን ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ቢሮውን ወክለው በሀዋሳ ከተማ ያስጀመሩት አቶ ዘገዬ ኩይሳ የቢሮ ምክትልና የጽ/ቤት ኃላፊ በሀገራዊ መርሃ ግብር መሠረት በክልሉ የመጀመሪያው ቀን የመማርና ማስተማር ሥራ መጀመሩን ጠቅሰው ዓመቱ ካለፈው ጊዜ የበለጠ ጥረት የምናደርግበትና የተሻለ ውጤት የምናስመዘግብበት እንድሆን ምኞታቸውን ገልጸው በክልሉ የ2018 ት/ዘመን ትምህርት በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።
የሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ደሳለኝ የትምህርት ሥርዓት በባህሪው በግዜ የተሸነሸነ በመሆኑ በሀዋሳ ከተማ ስር በሚገኙ በሁሉም በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ቀን የመማር ማስተማሩ ሥራ የተጀመረው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ለመላዉ ለክልላችን ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን ይሁን!